Fana: At a Speed of Life!

የካራማራ ድል ሉዓላዊነትን ለማስከበር ዋጋ የተከፈለበት ታላቅ ድል ነው – የቀድሞ ጦር ሠራዊት አባላት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የካራማራ ድል የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት ለማስከበር ዋጋ የተከፈለበት ታላቅ ድል መሆኑን የቀድሞ ጦር ሠራዊት አባላት ገለጹ።

ከዓድዋ ድል ጀምሮ በየዘመናቱ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ክብርና ሉዓላዊነት የማይደራደሩ መሆናቸውን በተግባር ካረጋገጡባቸው ታሪካዊ ሁነቶች መካከል ካራማራ አንዱ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ሠራዊት ክብርና ጀግንነት እስካሁንም መዝለቁን ገልጸው÷ ከሀገር አልፎ የአፍሪካ የሰላም ዘብ በመሆኑ የሁላችንም ኩራት ነው ብለዋል።

የካራማራ ድል ኢትዮጵያውያን ለወራሪ ኃይል መቼም ቢሆን እንደማይንበረከኩ ያረጋገጡበት መሆኑን ነው ለኢዜአ የተናገሩት፡፡

የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጀግኖች ወራሪውን የዚያድ ባሬ ጦር ካራማራ ላይ ድል ያደረጉበትና የኢትዮጵያ አሸናፊነት የታወጀበት ታሪካዊ ዕለት ዘንድሮ 46ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.