አቶ እንዳሻው ጣሰው በዱራሜ ከተማ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ የከረጢትና የማገዶ ከሰል ማምረቻ ፋብሪካዎችን እየጎበኙ ነው፡፡
በጉብኝቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በክልሉ ለሁለት ቀናት በሚቆየው የከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች የመስክ ምልከታ የተቀናጀ የግብርና ልማትና የኢንዱስትሪ ልማት እንቅስቃሴዎች እንደሚጎበኙ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡