Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 477 ሚሊየን ብር በመመደብ ገበያ የማረጋጋት ሥራ መከናወኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ገበያ ለማረጋጋት ከ259 ሺህ ኩንታል በላይ ምርትና ከ1 ነጥብ 7 ሚሊየን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ማቅረብ መቻሉን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ብዙአለም ግዛቸው÷ በክልሉ ገበያን ለማረጋጋት 477 ሚሊየን ብር መመደቡን ገልጸዋል።

በዚህም በዩኒየኖችና በህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት ከትርፍ አምራች አካባቢዎች እጥረት ወዳለባቸው ስፍራዎች ምርት በመውሰድ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲደርስ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ከ143 ሺህ 600 ኩንታል በላይ የሰብል ምርት፣ ከ88 ሺህ 100 ኩንታል በላይ የፋብሪካና ከ28 ሺህ ኩንታል በላይ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ማቅረብ መቻሉንም ገልጸዋል።

ከቀረቡት ምርቶች መካከል ጤፍ፣ በቆሎና የፉርኖ ዱቄት እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም እንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርት በማቅረብ ገበያውን ለማረጋጋት ጥረት ተደርጓል ብለዋል።

በስንታየሁ አራጌ

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.