ቢዝነስ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ማውን ከተማ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ

By Mikias Ayele

March 06, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቦትስዋና ማውን ከተማ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ።

አየር መንገዱ በረራውን ሰኔ 3 ቀን 2016 ዓ.ም የሚጀመር መሆኑን የገለፀ ሲሆን በሳምንት ሶስት ቀን ወደ ከተማዋ በረራ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡

አየር መንገዱ በረራ ሲጀምር ማውን ከተማ በቦትሰዋና ሁለተኛዋ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻ እንደምትሆን ተመላክቷል፡፡