የሀገር ውስጥ ዜና

በህዳሴ ግድብና በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ውይይት በባህር ዳር እየተካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

June 06, 2020

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህርዳር ዩኒቨርስቲ በታላቁ ህዳሴ ግድብና በአባይ ወንዝ ዙሪያ የምሁራን ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ የዩኒቨርስቲው ምሁራን ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዋና የህግ አማካሪ አቶ መርኸፅድ መኮንንና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።