Fana: At a Speed of Life!

ለዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር 4 ነጥብ 8 ቢሊየን ችግኝ ተዘጋጅቷል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ለዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በተለያዩ ችግኝ ጣቢያዎች 4 ነጥብ 8 ቢሊየን ችግኝ መዘጋጀቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የለውጡ መንግሥታችን የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን ቁልፍ ጉዳይ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም ስኬት በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና እንክብካቤ ላይ መንግስት በስፋት ተሰማርቶ እንደሚገኝ አንስተዋል።

የክልሉ መንግሥት ለተፋሰስ ልማትና ለአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ አንስተው፤ በዚህ ዓመት “የዜግነት አገልግሎት” በመጠቀም፣ በ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ የተፋሰስ ልማት ለመስራት ታቅዶ 98 በመቶ ማድረስ ተችሏል ብለዋል፡፡

በዓመቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር 5 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞን ለማዘጋጀት ታቅዶ በንቃት እየተሰራ ይገኛል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ እስካሁን በተለያዩ የችግኝ ጣቢያዎች 4 ነጥብ 8 ቢሊየን ችግኞችን ማዘጋጀት ተችሏል ሲሉ ገልጸዋል።

ይህም የዕቅዱ 87 በመቶ መሆኑን አመልክተዋል።

በቀሪው ጊዜ የተያዘውን የችግኝ ዝግጅት እቅድ ከማሳካት ጎን ለጎን የተከላ ቦታዎችን በጂፒኤስ የመለየትና የጉድጓድ ዝግጅት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.