በዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ንቅናቄዎች እንደሚደረግ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሴቶችን ከማሰብ ባለፈ ተጠቃሚነታቸውንና ተሳታፊነታቸውን የሚያረጋግጡ ንቅናቄዎች እንደሚደረጉ ተገለጸ፡፡
በኢትዮጵያ ለ48ኛ ጊዜ “ሴቶችን እናብቃ፤ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ሐሳብ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በማስመልከት የፓናል ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱም የሥርዓተ ጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ፣ የሥነ-ተዋልዶ ጤና ተደራሽነትን ለማስፋት፣ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ለመጨመር እና ከጾታዊ ጥቃት ነፃ የሆነች ኢትዮጵያን ለመፍጠር የተከናወኑ ሥራዎች ቀርበዋል፡፡
በዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ለብርቱ ሴቶች ዕውቅና እንደሚሰጥም የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አማካሪ ዘቢደር ቦጋለ ተናግረዋል፡፡
መንግሥት የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡና ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሚያስችሉ ሥራዎችን ማከናወኑንም አስረድተዋል፡፡
በመራኦል ከድር