Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤግዚቢሽን ላይ የቱሪዝም ሃብቶቿን እያስተዋወቀች ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በጀርመን በርሊን እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤግዚቢሽን ላይ የቱሪዝም ሃብቶቿን እያስተዋወቀች ነው፡፡

ሁለተኛ ቀኑን በያዘው በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ከተለያዩ ዓለምአቀፍ የጉዞ ድርጅቶችና የሀገራት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ዓለም አቀፍ አስጎብኚ ድርጅቶች ለደንበኞቻቸው ኢትዮጵያን እንደ አማራጭ እንዲያቀርቡና በጉዞ ዝርዝራቸው ውስጥ ማካተት በሚችሉበት ጉዳዮች ዙሪያ ተስማምተዋል፡፡

በተጨማሪም ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቱሪዝም ፕሮሞሽን እና ማርኬቲንግ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አድርገዋል::

ይህ በዓመቱ የሚዘጋጀው ኤግዚቢሽን በመላው ዓለም የሚገኙ ስመጥር የቱሪዝም ኩባንያዎች እና ሀገራት ያላቸውን መዳረሻ እና የቱሪዝም አገልግሎት የሚያስተዋውቁበት መድረክ ነው::

ኢትዮጵያም በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት እያከናውነች ያለችውን የመዳረሻ ልማት እና የቱሪስት መስህቦች እያስተዋወቀች እንደምትገኝ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.