የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ከሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

March 07, 2024

 

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ በአዲስ አበባ ከሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠ/ሚ ዐቢይ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳሉት ÷ “መዲናችን ከከተማ መስፋፋት ጋር የሚመጣ ፍላጎትን የሚያጎሉ ወሳኝ የሆኑ የእድገት እና የለውጥ ሂደት ውስጥ ትገኛለች።

የዛሬው ዓይነት ስብሰባዎች በሚታዩ ክፍተቶች የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ ብሎም መልካም አጋጣሚዎችን ለመለየት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡