ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ያላት አጋርነት ውጤታማ ሆኖ ቀጥሏል – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ያላት አጋርነት ውጤታማ ሆኖ መቀጠሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ዛሬ ማለዳ ባንኩ በኢትዮጵያ በሚያካሂዳቸው ፕሮጀክቶች ላይ በአፍሪካ ልማት ባንክ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ልማትና የቢዝነስ አቅርቦት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት አብዱል ካማራ (ዶ/ር) ጋር መወያየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አመልክተዋል።
በተጨማሪም ወንድሜ አኪንውሚ አዴሲና (ዶ/ር) የኦባፌሚ አዎሎው የአመራር ሽልማትን በማግኘቱ ይህን ዕድል ተጠቅሜ እንኳን ደስ ያለህ ለማለት እወዳለሁ ሲሉ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ላገኙት ሽልማት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።