Fana: At a Speed of Life!

የሴቶችን የዲጂታልና ፋይናንስ አካታችነት ማሳደግ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ስርዓተ-ፆታ ልዩነትን ለማጥበብ እና የሴቶችን የዲጂታል አካታችነት ማሳደግ የሚያስችል ስምምነት ከጂ ኤስ ኤም ኤ ጋር ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እና የጂ ኤስ ኤም ኤ አመራሮች በስፔን ባርሴሎና ተፈራርመዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ሴቶች በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ልማት ዘርፈ ብዙ እና ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡

የዲጂታል ስርዓተ-ፆታ ክፍተት ለመቀነስ የሞባይል ኢንተርኔትና የሞባይል ፋይናንሺያል አገልግሎቶችን ለሴቶች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ስምምነቱ በኢትዮጵያ የሴቶችን የሞባይል ኢንተርኔት እና የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት (ቴሌብር) ተጠቃሚ ቁጥር በፈረንጆቹ እስከ 2026 በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያለመ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኩባንያው ለተግባራዊነቱ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ እና በመተግበር ሴቶች የሚያጋጥሟቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መፍታት ላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ አስተድረዋል፡፡

አሁን ላይ የሴቶች የዲጂታል ተጠቃሚነት በተለይም ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ከወንዶች አንጻር ሴቶች በሰባት በመቶ ያነሰ የሞባይል ስልክ እና 19 በመቶ ያነሰ የሞባይል ኢንተርኔት የመጠቀም ዕድል እንዳላቸው ተመላክቷል፡፡

የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት የመጠቀም ዕድላቸው ደግሞ ከ28 በመቶ ያነሰ መሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.