Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

ቀኑ “ሴቶችን እናብቃ፣ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ የሚገኘው፡፡

በመርሐ ግብሩ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ የመስኖና ቆላማ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) እና ሌሎች እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓለም ለ113ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ ነው በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ የሚገኘው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.