Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነት ማረጋገጥ ተጨማሪ ሥራ ይፈልጋል አሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና እኩል ተሳታፊነት ማረጋገጥ ብዙ ክፍተት ስላለበት ተጨማሪ ጥረትና ሥራ እንደሚፈልግ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስገነዘቡ፡፡

“ሴቶችን እናብቃ፣ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ!” በሚል መሪ ሐሳብ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተከብሯል፡፡

ዕለቱን አስመልክቶ ከንቲባዋ ባስተላለፉት መልዕክት÷ የሴቶችን መብትና የፆታ እኩልነት በማረጋገጥ በሀገራችን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የልማት ተሳትፎዎች ላይ ያላቸውን ድርሻ ለማሳደግ በሁሉም ዘርፍ እየሠራን ነው ብለዋል።

ይሁን እንጂ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና እኩል ተሳታፊነት ማረጋገጥ ብዙ ክፍተት ስላለበት ተጨማሪ ጥረትና ስራ ይፈልጋል ነው ያሉት።

ይህን ክፍተት ማጥበብ ደግሞ ከማንም በላይ እድሉን አግኝተን ሀገር እየመራን ካለነው ሴት የፖለቲካ አመራሮች ይጠበቃል ብለዋል።

እኛ በተሰማራንበት ውጤታማ ከመሆን አልፈን እድሉን ላላገኙ ሴቶች ምሣሌዎች፣ በር ከፋቾች፣ ማበረታቻዎችና እንደሚችሉ ማሳመኛ መረጃና ማስረጃዎች መሆን እንችላለን ሲሉም ገልጸዋል።

ከዚህም አልፎ የሴቶች ተጠቃሚነትንና ሁለንተናዊ ተሳትፎን ለማረጋገጥ የሚችሉ ተጨባጭ ስራዎችን የመስራት ኃላፊነት አለብን በማለት አስገንዝበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.