Fana: At a Speed of Life!

በፖሊሳዊ ግዳጆች የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ አመራሮችና አባላት እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ በተለያዩ ፖሊሳዊ ግዳጆች የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ አመራሮችና አባላት የእውቅናና የሽልማት መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

እውቅናና ሽልማቱ ፖሊሳዊ ግዳዳጆችን በአገር ፍቅር ስሜትና ጀግንነት ለተወጡ አመራሮችና አባላት እንደሆነ ተጠቁሟል።

በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል፣ የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነሮች፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን ኮሚሽነር፣ የፌዴራል ፖሊስ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ÷ የፌዴራል ፖሊስ የተሰጠውን ሀገራዊ ግዳጅ በጀግንነት እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

ሕገ-መንግሥቱ ለዜጎች የሰጠው መብት እንዳይሸራረፍ ፖሊስ አበክሮ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው የዜጎች ሰላምና ደኅንነት እንዲረጋገጥም ፖሊስ ኃላፊነቱን በጀግንነት እየተወጣ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በአፍሪካ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም የመሆን ራዕይን አንግቦ እየሰራ መሆኑንም ገልጸው÷ ለዚህም ዘመኑን በዋጁ ትጥቆች፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እንዲሁም በሰለጠነ የሰው ኃይል መደራጀቱን ቀጥሏል ነው ያሉት።

በዚህም የፖሊስ የማድረግ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን አመላክተዋል።

በበረከት ተካልኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.