Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል ከ400 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ከ400 ሚሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹን የመረቁት÷ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ እና የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው፡፡

ፕሮጀክቶቹ ገጠርን ከከተማ በማቆራኘት ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴዎችን ያሳድጋሉ ተብሏል።

ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል የአስፋልት መንገድ፣ ትምህርት ቤቶችና ሌሎች ለማህበራዊ አገልግሎት መስጫ የሚውሉ ተቋማት እንደሚገኙበት ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.