የሀገር ውስጥ ዜና

ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከባስኬቶ ዞን ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

By Amele Demsew

March 09, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ከባስኬቶ ዞን ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ዞኑ ጤፍ፣ በቆሎ፣ ሰሊጥ፣ ሩዝ፣ ኮረሪማና ሌሎች የግብርና ምርቶችን በብዛት አምራች ቢሆንም ምርቶችን ወደ ገበያ ለማውጣት የመንገድ ችግር መኖሩን ተሳታፊዎች አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም የንጹህ የመጠጥ ውኃና የኤሌክትሪክ አቅርቦት ችግርን ጨምሮ ሌሎች አሉ ያሏቸውን ችግሮች ገልጸዋል፡፡

ርዕሠ መሥተዳድሩ በሰጡት ምላሽም÷ ክልሉ የሰላም፣ የመቻቻል እና የብልፅግና ተምሳሌት እንዲሆን ባለፉት 6 ወራት በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዞኑ ተስፋ ሰጪ ለውጦች እየታዩ መሆናቸውን ጠቅሰው÷ በተሳታፊዎች የተነሱትን ጥያቄዎች ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችንም ቅድሚያ የሚሰጠውን በማስቀደም ችግሮችን በሂደት ለመፍታት እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

በኢብራሂም ባዲ

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!