ስፓርት

ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ መድንን 2 ለ 0 አሸነፈ

By Mikias Ayele

March 09, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ መድንን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

10፡00 ሠዓት ላይ በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የፋሲል ከነማን የድል ጎሎች ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት እና ናትናኤል ማስረሻ በጨዋታ አስቆጥረዋል፡፡

ውጤቱን ተክትሎም አፄዎቹ ነጥባቸውን ወደ 29 ከፍ በማድረግ 4ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ÷ ኢትዮጵያ መድን በነበረበት 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ምሽት 1፡00 ሠዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዳዊት ተፈራ (2) እና ቢንያም በላይ ጎሎች ሀምበሪቾ ዱራሜን 3 ለ 1 ረትቷል፡፡

የሀምበርቾን ብቸኛ ጎል ደግሞ ቶሎሳ ንጉሴ አስቆጥሯል፡፡