የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በሦስት ደንቦች ላይ ተወያይቶ አጸደቀ

By Mikias Ayele

March 09, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ካቢኔ ባካሄደው 3ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ስብሰባ በሦስት የከተማዋ ደንቦች ላይ ተወያይቶ አጽድቋል፡፡

ደንቦቹም÷

1ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የበጎ ፈቃድ አስተዋፅኦን፣ አገልግሎት እና ማኅበራዊ ኃላፊነት አሠራር ለመደንገግ ተዘጋጅቶ የቀረበው ረቂቅ ደንብ፤

2ኛ. የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሚመሩበትን ሥርዓት እንደገና ለመወሰን የተዘጋጀውን ረቂቅ ደንብ  እና

3ኛ. የዓድዋ ድል መታሰቢያ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብን መርምሮ ከተወያየ በኋላ ለተሻለ የአሠራር ሥርዓት እንዲያመቹ በማድረግ የሕግ ማዕቀፍ ላይ ተወያይቶ ማጽደቁን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡