Fana: At a Speed of Life!

ሕዝበ ክርስቲያኑ የዐብይ ፆም ሲፆም መጣላትና መለያየትን በመተው ሊሆን ይገባል- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝበ ክርስቲያኑ ታላቁን የዐብይ ፆም ሲፆም መጣላትን፣ መለያየትንና መገፋፋትን እርም ብሎ በመተው ሊሆን ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አሳሰቡ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ታላቁ የዐብይ ፆምን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸው ÷ጾም ማለት እህልንና የእንስሳት ውጤቶችን ከመመገብ መከልከል ብቻ አይደለም ያሉ ሲሆን ከዚህ ባሻገር እኩይ ነገሮችን ላለማስተናገድም መወሰን ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

“ስንጾም መጣላትን፣ መለያየትና መገፋፋትን እርም ብለን መተው እና በጎ ነገርን ለመስራት በእጅጉ መበርታት ይጠበቅብናልም” ነው ያሉት፡፡

ዲያብሎስ ተስፋ ቆርጦ የሚሸሸው ይቅር ስንባባል፤ ለሰላምና ለአንድነት፣ ለፍቅርና ለስምምነት ስንቆም ነው ማለታቸውን ከኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፆማችን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ወደ ቀያቸው ተመልሰው ሰላማዊ ኑሮ መኖር ሲችሉ፣ የተራቡት ሲደገፉ እንደሆነ ያነሱት ፓትርያርኩ ለዚህም ሕዝበ ክርስቲያኑ ታላቁን የዐብይ ፆም ሲፆም ለተቸገሩ ወገኖቹ ያለውን በማካፈል ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.