Fana: At a Speed of Life!

ለውጭ ገበያ ከቀረበ የእንስሳት ክትባት 665 ሺህ ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት ባለፉት ሰባት ወራት ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለገበያ ካቀረበው የእንስሳት ክትባት 665 ሺህ ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገለፀ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ታከለ አባይነህ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ኢንስቲትዩቱ 23 ዓይነት የእንስሳት ክትባት እያመረተ ይገኛል።

ክትባቶቹንም ለሀገር ውስጥ ፍጆታ እንዲሁም ቀሪውን ደግሞ ወደ ተለያዩ የምዕራብና ማዕከላዊ አፍሪካ ሀገራት እያቀረበ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም ባለፉት ሰባት ወራት 175 ሚሊየን ዶዝ ክትባት ለውጭ ገበያ በማቅረብ 665 ሺህ ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልፀዋል።

ኢንስቲትዩቱ ክትባቱን ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በማስተዋወቅ የገበያ ተደራሽነቱን ለማስፋት እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በሀገር ውስጥም ወደ ተለያዩ ክልሎች ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ ባለሃብትች በዘርፉ እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢንስቲትዩቱ በዓመት ወደ 350 ሚሊየን ዶዝ ክትባት ቢያመርትም የሀገር ውስጥንና የውጭ ተጠቃሚዎችን የክትባት ፍላጎት የሚያሟላ አይደለም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በመሆኑም የአቅርቦት ችግሩን ለመፍታት ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን ቀርፆ ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ነው ያስረዱት።

ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የእንስሳት መድኃኒቶች የምዝገባና ፈቃድ ሥራ እየሰራ መሆኑን አንስተው፤ ምርቶች የማስተዋወቅ ሥራም ጎን ለጎን እየተከናወነ እንደሆነ ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.