የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮ ማልታ ኢንቨስትመንት ፎረም ተካሄደ

By Feven Bishaw

March 12, 2024

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው ኢትዮ ማልታ ኢንቨስትመንት ፎረም ተካሂዷል፡፡

ፎረሙ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የማልታ የኢንቨስትመንት እና የንግድ ፕሮሞሽን ተቋም ከሆነው ከትሬድማልታ እና ከኢትዮጵያ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ፎረሙ ሁለቱ ሀገራት በጤና፣ በአይሲቲ፣ በትምህርት፣ በኮንስትራክሽን ፣ቱሪዝም፣ ማዕድንና በሌሎች ዘርፎች ላይ በሚኖራቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀ ነው ተብሏል ።

በትእግስት አስማማው