የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ ያካሂዳል

By Feven Bishaw

March 12, 2024

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ በአርባምንጭ ከተማ ማካሄድ ይጀምራል፡፡

በጉባኤው 19 አዋጆች እና አንድ ደንብ ላይ የምክር ቤቱ አባላት ተወያይተው እንደሚያፀድቁ ይጠበቃል ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዲስ ክልል እንደመሆኑ ለቀጣይ ስራ የሚያግዙ አሰራርና አዋጆች በጥልቀት እንደሚገመገሙ ነው የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ፀሐይ ወራሳ የገለፁት፡፡

በማቲዎስ ፈለቀ