የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበረከቱ

By Shambel Mihret

March 12, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደ ደማቅ ስነ-ስርዓት ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበርክተዋል።

በሽልማቱ የከበሩት ተቋማት የግብርና ሚኒስቴር/በስንዴ ልማት ፕሮግራም/፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ናቸው።

ተቋማቱ የኢትዮጵያ የእድገት እና የፈጠራ ልክ ማሳያ የሆኑ ምልክቶች መሆናቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡