ስፓርት

ራፋኤል ቤኒቴዝ ከሴልታ ቪጎ አሰልጣኝነታቸው ተሰናበቱ

By Feven Bishaw

March 12, 2024

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ራፋኤል ቤኒቴዝ ከስፔኑ ሴልታ ቪጎ ቡድን አሰልጣኝነታቸው ተሰናብተዋል፡፡

የሊቨርፑልና የቼልሲ የቀድሞ አሰልጣኝ የነበሩት ቤኒቴዝ የላሊጋውን ቡድን በአሰልጣኝነት የተረከቡት ባለፈው ሰኔ ወር ነበር፡፡

ሴልታ ቪጎ በራፋኤል ቤኒቴዝ አሰልጣኝነት ወቅት ካደረጋቸው 28 የላሊጋ ጨዋታዎች ውስጥ ማሸነፍ የቻለው 5ቱን ብቻ ነው፡፡

ሴልታ ቪጎ በላሊጋው የደረጃ ሰንጠረዥ በ24 ነጥብ በ17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡