Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ጥሪ ተቀብለው የተሃድሶ ስልጠና ለገቡ የቀድሞ የአማራ ልዩ ሃይል አባላት አቀባበል ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል የጠራውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ለሁለተኛ ዙር የተሃድሶ ስልጠና ለገቡ የቀድሞ የአማራ ልዩ ሃይል አባላት አቀባበል ተደረገላቸው።

በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ኮሎኔል አየለ ጊሳ÷ በተሃድሶ ሥልጠናው የሚፈጠርላችሁን አቅም ወደ ታች አውርዳችሁ መሬት እንዲነካ ማድረግ ይጠበቅባችኋል ብለዋል።

ክፍተቶችን እየተጠቀመ ክልሉን ሰላም እየነሳ ያለውን ጽንፈኛ ቡድን በማጥፋት የሕግ የበላይነት እንዲከበር ተግባር ተኮር ሥራ ይጠበቅባችኋል ሲሉም አስገንዝበዋል።

እስከ ህይወት መስዋዕትነት የሚዘልቅ ቁርጠኝነት በማሳየት ፅንፈኛውን ቡድኑን በአጭር ጊዜ በማፅዳት የክልሉን ሰላም ማረጋገጥ የዚህ ሃይል ዋነኛ ተልዕኮ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት፡፡

የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ም/ ሃላፊ አቶ በሪሁን መንግስቱ÷ የኢትዮጵያን ታላቅነት የማይፈለጉ ጠላቶቻችን በተራዘመ የሴራ ፖለቲካ ከውስጥ እና ከውጭ ትስስር ፈጥረው መዋቅራዊ በሆነና ባልሆነ መንገድ እረፍት አልባ የጥላቻ ቅስቀሳ ስራ  እያከናወኑ ነው ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡

ወደ ከፋ ባርነት እና መመለሻ ወደሌለው የድህነት አዙሪት ውስጥ የሚከትና የተሳሳተ የትግል አውድ ውስጥ መሆናችሁን አውቃችሁ ከዚህ ተልዕኮ መውጣታችሁ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ሲሉም  ተናግረዋል፡፡

ጽንፈኛውን ቡድን በአጭር ጊዜ በማፅዳት የክልሉን ሰላም ማረጋገጥ እንደሚገባ መናገራቸውንም  የክልሉ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.