ለ ‘አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ’ የተመደበው በጀት ለግል ጥቅም በመዋሉ ፓርቲው ታግዶ ምርመራ እንዲካሄድ ውሳኔ ተላለፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 ዓ.ም ለ‘አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ’ በምርጫ ቦርድ የተደረገለት የበጀት ድጋፍ ለታለመለት ዓላማ ሳይውል ለግል ጥቅም መዋሉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡
ፓርቲው የበጀት ድጋፉን ለታለመለት ዓላማ እንዳላዋለ እና ከፍተኛ ገንዘብ በፓርቲው አመራሮች እና ሌሎች አባላት ለግል ጥቅም እንዲውል መደረጉን እንደተገነዘበ ቦርዱ ገልጿል።
በመሆኑም ፓርቲው እና አመራሮቹ እንዲታገዱ፤ ተገቢው የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር እና ያለአግባብ ወጪ የሆነውን ገንዘብ በተመለከተ የፍ/ብሄር ክስ እንዲመሰረትና ገንዘቡ ለቦርዱ ተመላሽ እንዲደረግ ቦርዱ ውሳኔ አሳልፏል፡፡