Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና ፓኪስታን ሁለንተናዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና ፓኪስታን መካከል ያለው ሁለንተናዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የውጭ ግንኙትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር አቲፍ ሸሪፍ ጋር በሁለቱ ሀገራት ሁለንተናዊ ግንኙነት ዙሪያ መክሯል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር)÷ የኢትዮጵያ እና የፓኪስታን ሁለንተናዊ ትስስር ታሪካዊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሀገራቱን ሕዝቦች በንግድ፣ በጤና፣ በኢንቨስትመንት፣ በባህልና በቴክኖሎጂ ሽግግር በማስተሳሰር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል፡፡

አምባሳደር አቲፍ ሸሪፍ በበኩላቸው÷ በሀገራቱ መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት፣ ትምህርት፣ ኢኮኖሚ፣ ባህል፣ ቱሪዝምና ዲፕሎማሲያዊ ትስስር ለማጠናከር ጥረት እንደሚደረግ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በትምህርት፣ በጤና እና በኢንቨስትመንት ልማት ዘርፍ ፓኪስታናውያን ባለሃብቶች እና ምሁራን በስፋት እየሰሩ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይ ይህንን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰራ አጽንኦት መስጠታቸውንም የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

የሀገራቱን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባዔዎች ከፓኪስታን የፓርላማ አባላት ጋር የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉም ጋብዘዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.