ምክር ቤቱ ነገ 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን እንደሚያካሂድ አስታውቋል፡፡
በስብሰባውም የአንድ የምክር ቤት አባል ያለመከሰስ መብት እንደሚነሳ ይጠበቃል መባሉን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ዘጠኝ ረቂቅ አዋጆችን እንደሚያጸድቅ እና ሁለት ረቂቅ አዋጆችን ደግሞ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች እንደሚመራ ይጠበቃል።