የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩትና ዩኤንዲፒ በትብብር ለመስራት ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ ከተመድ የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) የኢትዮጵያ ተወካይ ሳሙኤል ባይድ ዶው (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ ሁለቱ ተቋማት በጋራ እና በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩትን ተልዕኮና በትኩረት የሚሰራባቸውን ጉዳዮች አስመልክተው ገለጻ ያደረጉት አቶ ጃፋር በድሩ፤ ኢንስቲትዩቱ በጥናትና ምርምር፣ በፖሊስ አቅጣጫዎችና አቅም ግንባታ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አንስተዋል፡፡
ሳሙኤል ባይዴ ዶው (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ዩኤንዲፒ ከውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ጋር በዘላቂ ልማት እና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡
ተቋማቱ በጋራ ጉዳዮች ላይ በትበብር ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡