ከትግራይ ክልል የተወጣጡ የሕብረተሰብ ተወካዮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሁሉም የትግራይ ክልል አካባቢዎች የተወጣጡ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡
ተወካዮቹ የጋራ የድል ታሪካችን የሆነው የዓድዋ ድል መጪውን ትውልድ በሚያስተምር፣ በሚያስተሳስርና ታሪኩን በጠበቀ መልኩ የዓድዋ ድል መታሰቢያ በመገንባቱ እንደተደሰቱ መግለጻቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡