የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከትግራይ ክልል የሕብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

March 15, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትግራይ ክልል የተለያዩ የሕብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ የዛሬው ውይይት ከትግራይ ክልል ተጉዘው ከመጡ የሕብረተሰብ ተወካዮች ጋር በተለያዩ ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ የተካሄደ ነበር ብለዋል።

በትግራይ ክልል ሰላም እና ልማትን ለማስገኘት ያለን ቁርጠኝነት ሁልጊዜም ጽኑ ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የዛሬው ውይይታችንም ይህንኑ የጋራ ዓላማ ለማሳካት የበለጠ ድጋፍ የሚሰጥ ነበር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፡፡