ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከሞሪታንያ ኢስላሚክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት የተላከላቸውን መልዕክት ተቀበሉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሞሪታንያ ኢስላሚክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ኦልድ ቼክ ኤል ጋዙዋን የተላከላቸውን መልዕክት ተቀበሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ከሞሪታንያ ኢስላሚክ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና የትብብር ሚኒስትር ሞሃመድ ሳሌም ኦልድ ሜርዙግ (ዶ/ር) ጋር በጽሕፈት ቤታቸው መወያየታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በዚህ ወቅትም ከሞሪታንያ ኢስላሚክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ኦልድ ቼክ ኤል ጋዙዋን የተላከላቸውን መልዕክት መቀበላቸውን ገልጸዋል፡፡