የሀገር ውስጥ ዜና

የዓድዋ መታሰቢያ የሚጎበኝበት ዋጋ ዝርዝር ይፋ ሆነ

By Feven Bishaw

March 15, 2024

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት የሚሆነው የዓድዋ መታሰቢያ የሚጎበኝበት ዋጋ ዝርዝር ይፋ ሆነ።

የጀግኖች ምስለ ቅርፅና ድሉን የሚያወሱ ቁሳቁሶችን በመታሰቢያው ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናሉ።

የክፍያ አማራጮች በቴሌ ብር፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በተቋሙ ድረገፅ የሚከናወን ደግሞ በማንኛውም የባንክ አማራጭ መክፈል እንደሚቻል የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ውባየሁ ማሞ (ኢ/ር) ገልፀዋል።

በዚህም መሰረት ለመደበኛ 150፣ ለተማሪዎች 75 እና ለልዩ ልዩ 550 ብር እንደሆነ ተገልጿል።

መታሰቢያው ከ2:30 እስከ 11:30 ሰዓት ተኩል ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናል ተብሏል።

በታሪኩ ወ/ሰንበት