Fana: At a Speed of Life!

በማሌዢያ የሚኖሩ ሩሲያውያን በሀገራቸው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ድምጽ ድምጽ እየሰጡ መሆኑ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማሌዢያ የሚኖሩ ሩሲያውያን በሀገራቸው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ድምጽ ድምጽ እየሰጡ መሆናቸውን በማሌዢያ የሩሲያ አምባሳደር ኔይል ላቲፖቭ ገለጹ።

በፈረንጆቹ ከመጋቢት 15 እስከ 17 ቀን 2014 እየተካሄደ ባለው የሩሲያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከሀገሪቱ ውጪ ባሉ ሀገራት በርካታ የሩሲያ ማህበረሰብ ባለባቸው ሀገራት ድምጽ እንደሚሰጥም ጠቁመዋል።

ማሌዢያ በርካታ ሩሲያውያን ያሉባት ሀገር መሆኗን ጠቅሰው፤ በዚያ የሚኖሩ ሩሲያውያን ድምጽ የሚሰጡበት ዕድል መፈጠሩን አመልክተዋል።

በዚህም በማሌዢያ በሚገኘው የሩሲያ ፌዴሬሽን ኤምባሲ ተገኝተው ዜጎቹ ለሚመርጡት ፕሬዚዳንት ድምጽ መስጠታቸውን ገልጸዋል።

ለቀጣይ ስድስት የስራ ዓመታት ሩሲያን ለማስተዳደር በሚደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አራት እጩዎች እየተፎካከሩ ሲሆን በስልጣን ላይ ያሉት ቭላድሚር ፑቲን፣ የቀኝ ክንፍ ሊበራል ዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪ ሊዮኒድ ስሉትስኪ፣ የኮሚኒስት እጩ ኒኮላይ ካሪቶኖቭ እና የሊበራል ማእከላዊ አዲስ ህዝቦችን የሚወክሉት ቭላዲላቭ ዳቫንኮቭ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ናቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.