Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና በነጻ እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና በነጻ እየተሰጠ ነው።

ሕክምናው በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከኩሓ ሆስፒታልና ሂማሊያን ‘ካታራክት’ ከተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው እየተሰጠ የሚገኘው።

የ’ሂማሊያን ካታራክት’ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ተስፋይ ተክለማሪያም÷ተቋማቱ በዚህ ዓመት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ሕክምና በቅንጅት እየሰጡ ነው።

በዚህ መሰረትም በክልሉ ደቡባዊ ዞን በማይጨው ለምለም ካርል ሆስፒታል ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ለተወጣጡ ከ800 በላይ ህሙማን አገልግሎቱን ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

”በሚድን የዓይን ሕመም ምክንያት ህዝባችን ለአይነ ስውርነት መዳረግ የለበትም” ያሉት አስተባባሪው÷በቀጣይ በክልሉ ሌሎች ዞኖች አገልግሎቱ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በማይጨው ለምለም ካርል ሆስፒታል የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና ባለሙያ አቶ የማነ ግተት በበኩላቸው÷ በሆስፒታሉ ህክምና የተደረገላቸው ወገኖች አስፈላጊው ክትትል እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.