የሀገር ውስጥ ዜና

የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተለያዩ ክልሎች የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

By ዮሐንስ ደርበው

March 18, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በተለያዩ ክልሎችና ከተማ አሥተዳደሮች የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተመለከተ።

መንግስት በሁሉም ክልሎች ያሉ ሃብትና ጸጋዎችን በአግባቡ ለመጠቀም እንዲቻል፣ የሚነሱ ቅሬታዎችንም ከኀብረተሰቡ ጋር ተቀራርቦ ለመፍታት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ አመራሮችም በተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እያደረጉት ያለው የመስክ ምልከታና ድጋፋዊ ክትትል መርሐ-ግብር የዚህ ተግባር አካል መሆኑ ተጠቁሟል።

አመራሮቹ በጉብኝታቸው÷ የበጋ መስኖ ሥንዴ ልማት፣ የተፈጥሮ ሐብት ልማትና ጥበቃ ሥራ፣ የሌማት ትሩፋት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡