ስፓርት

አትሌት ሳሙኤል ፍሬው በ3 ሺህ ሜትር መሰናከል የመጀመሪያውን ወርቅ ለሀገሩ አስገኘ

By Melaku Gedif

March 18, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ወንዶች አትሌት ሳሙኤል ፍሬው የመጀመሪያውን ወርቅ ለኢትዮጵያ አስገኝቷል፡፡

አትሌት ሳሙኤል ርቀቱን 8 ደቂቃ 24 ሰከንድ ከ30 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነው፡፡

በመርሐ ግብሩ የ5 ሺህ ሜትር የሴቶች ፍፃሜ ውድድር ሲካሄድ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች እንደሚጠበቁ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡