የጠ/ሚ ጽ/ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ጽ/ቤት የአካቶ ትግበራ አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የሴቶች እና ማህበራዊ ጽሕፈት ቤት የአካቶ ትግበራ አባላት እና የአንድነት ፓርክ ሰራተኞች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች እንዳሉት÷ መታሰቢያው ከዓድዋ ድል መታሰቢያነቱ በተጨማሪ ሁሉን አቀፍ አገልግሎቶችን በውስጡ አካትቶ ይዟል፡፡
ይህም ለወጣቱ ትውልድ በቀላሉ ታሪክን ለማስገንዘብና ለማስተላለፍ ትልቅ አቅም ይሆናል ማለታቸውን የድል መታሰቢያው መረጃ ያመላክታል፡፡