የአየር ሃይል አመራሮችና አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

By Melaku Gedif

March 20, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ አየር ሃይል አመራሮች፣ አባላትና ሲቪል ሰራተኞች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች÷ የዓድዋ ድል መታሰቢያ የኢትዮጵያዊያን የተጋድሎ ታሪክ መዘከሪያ ብቻ ሳይሆን ለአዲሱ ትውልድ የሀገር ፍቅር ስሜትን የሚፈጥር ሁነኛ መነሳሻም ነው ብለዋል፡፡

ኮሎኔል መኳንንት ደሳለኝ እና ሻምበል ሰለሞን በየነ÷ በዓለም የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ደማቅ አሻራ ያለውን ታላቁ የዓድዋ ድል ለመዘከር የተገነባውን መታሰቢያ መጎብኘት ብቻውን ልዩ የመንፈስ እርካታ እንዳለው አንስተዋል፡፡

በተለይም ለሠራዊት አባላት ትርጉሙ ብዙ እንደሆነ መግለጻቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡