ስፓርት

በ3 ሺህ ሜትር የሴቶች መሰናክል ውድድር ኢትዮጵያ የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች

By ዮሐንስ ደርበው

March 20, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ3 ሺህ ሜትር የሴቶች የመሰናክል ውድድር ኢትዮጵያ በአትሌት ሎሚ ሙለታ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡

አትሌቷ 9 ደቂቃ 26 ሰከንድ ከ63 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው 3ኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው፡፡

እንዲሁም አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ እና ፍሬሕይወት ገሰሰ 4ኛ እና 5ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀዋል፡፡

ይህን ውድድር ኬንያዊቷ ቢያትሪስ ቼፕኮዪች 9 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ ከ61 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ክብረወሰን በማስመዝገብ ጭምር ስታሸንፍ÷  ኡጋንዳዊቷ ፔሩዝ ቼሙታይ ሁለተኛ ሆናለች፡፡

በሰለሞን በቀለ