በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ባሕር ዳር ከተማ ሊገባ የነበረ 25 ሺህ የሽጉጥ ጥይት ተያዘ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ባሕር ዳር ከተማ ሊገባ የነበረ 25 ሺህ የሽጉጥ ጥይት እና አንድ ሽጉጥ መያዙ ተገለጸ፡፡
የተያዘው ጥይት መነሻውን ከሱዳን ጠረፍ አድርጎ በጎንደር መሥመር በኩል ወደ ባሕር ዳር ከተማ ሊገባ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን÷ ለፅንፈኛው ኃይል ሊተላለፍ እንደነበርም ተመላክቷል፡፡
በመሆኑም በመከላከያና በደኅንነት ኃይሎች የተቀናጀ ክትትል መያዙን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡