ስፓርት

ኢትዮጵያ በሴቶች የቦክስ ውድድር 2 የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

By Tamrat Bishaw

March 22, 2024

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋና እየተካሄደ ባለው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በ52 እና በ66 ኪሎ ግራም ሴቶች የቦክስ ውድድር 2 የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች።

ቤተልሔም ገዛኸኝ ለሀገሯ የወርቅ ሜዳሊያ ያመጣችው በፍጻሜ ውድድሩ የሞሮኮዋን ቼዳል ራባብ 4ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው።

በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊቷ ቦክሰኛ ቤተልሔም ወልዴ በ66 ኪሎ ግራም ከሞዛምቢኳ ቡጢኛ ጋር ለፍፃሜ ተገናኝታ በቦክስ ስፖርት ለኢትዮጵያ 2ኛ የወርቅ ሜዳልያ አስገኝታለች፡፡