ስፓርት

ኢትዮጵያ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ሩጫ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

By Tamrat Bishaw

March 22, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋና እየተካሄደ ባለው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ሩጫ ውድድር በሀጎስ ገብረህይወት አማካኝነት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች።

አትሌት ሀጎስ ገብረህይወት 13:38.12 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ውድድሩን በቀዳሚነት አሸንፏል።