የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለአብርሆት ቤተ -መጻሕፍት 2 ሺህ መጻሕፍት አበረከተ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት የተለያየ ይዘት ያላቸውን 2 ሺህ መጻሕፍትን አበርክቷል።
ኮሌጁን በመወከል መጻሕፍቱን ያበረከቱት የኮሌጁ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ልዑል ከበደ÷ የተበረከቱት መጻሕፍት ቤተ-መጻሕፉ በንባብ ልምዱ የበለፀገና በዕውቀት የታገዘ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት የሚያደርገውን ጥረት ያግዛሉ ብለዋል፡፡
ኮሌጁ የንባብ ባህሉ የዳበረ ሀገር ተረካቢ ትውልድ በማፍራት ላይ ለሚገኘው የአብርሆት ቤተ -መጻሕፍት የሚያደርገውም ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አዛዡ አረጋግጠዋል።
የአብርሆት ቤተ -መጻሕፍት ቴክኒክ ቡድን አስተባባሪ አቶ ደርብ እርገጥ ኮሌጁ ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡