የባህር ሃይል ጠቅላይ መምሪያ አባላት የአድዋ ድል መታሠቢያን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህር ሃይል ጠቅላይ መምሪያ አባላት የአድዋ ድል መታሠቢያን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የባህር ሃይል አባላት የአድዋ ድል ዘመን ተሻጋሪ መሆኑን ገልፀው÷ ታሪካዊ የሆነውን መታሠቢያ በመጎብኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
እንዲሁም የአድዋ ድል መታሠቢያ ብዙ ታሪካዊ እውነታዎችን የያዘ መሆኑን የገለፁ ሲሆን÷ በመጎብኘታቸው ልዩ ስሜት እንደፈጠረባቸው መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡