Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ሰራተኞች የሚገለገሉበት አዲስ የደንብ ልብስ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች የሚገለገሉበት አዲስ የደንብ ልብስ በዛሬው እለት ይፋ ሆኗል።

ይፋ የሆነው የደንብ ልብስ በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እየተካሄደ ባለው ተቋማዊ ሪፎርም ስልጡን፣ ዘመናዊ እና ስነ-ምግባር የተላበሰ ሲቪል ሰራተኛ የመፍጠር አካል ነው ተብሏል፡፡

በስነ-ስርአቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን÷ ኤጀንሲው የአገልግሎት አሰጣጡን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስና የህብረተሰቡን እርካታ ማረጋገጥ ይኖርበታል ብለዋል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በበኩላቸው÷ የደንብ ልብሱ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ ሰራተኞች ለብሰውት ዘመናዊ እና ስነ-ምግባር የተላበሰ አገልግሎት እንዲሰጡ ታሳቢ አድርጎ መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡

ተቋሙ የተሰጠውን ሃላፊነት እንዲወጣም ሰራተኛው በገባው ቃል መሰረት በቅንነት እና በታማኝነት አገልግሎት እንዲሰጥ አስገንዝበዋል፡፡

በስራ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የኤጀንሲው ሰራተኞች የእውቅና መርሐ- ግብርም ተከናውኗል።

በትዝታ ደሳለኝ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.