ስፓርት

በ45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው ቡድን የማጠቃለያ ልምምድ አከናወነ

By Shambel Mihret

March 23, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰርቢያ ቤልግሬድ በሚካሄደው 45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው ቡድን የማጠቃለያ ልምምዱን ዛሬ አከናወነ።

ከሳምንት በኋላ በፈረንጆቹ መጋቢት 30 ቀን 2024 በሚካሄደው ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የአትሌቲክስ ቡድን ጠንካራ ልምምድ ሲያካሂድ መቆየቱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመልክቷል።

ቡድኑ ዛሬ የመጨረሻ ልምምዱን በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ያካሄደ ሲሆን፤ በዚህም የትራክ ልምምድ በተጠናከረ መልኩ መስራቱ ተገልጿል።