Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን በሚኖሩበት ሀገር የሀገራቸው አምባሳደር ናቸው – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን በሚኖሩበት ሀገር የሀገራቸው አምባሳደር ናቸው ሲሉ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቷ በግሪክ ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በወቅቱም ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩበት ሀገር የሀገራቸው አምባሳደር በመሆናቸው ያለምንም ልዩነት ለኢትዮጵያ ጥብቅና መቆም እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በውጭ ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን የቆንስላ አገልግሎቶችን ለመስጠት አቅም በፈቀደ መጠን ጥረት የሚደረግ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኤምባሲ በሌለባቸው አካካቢዎች የሚኖሩ ዜጎችን ጉዳይ በቅርብ ባሉ ኤምባሲዎች ለመሸፈን በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ተቀማጭነታቸው በሮም ሆኖ በግሪክ የኢትዮጵያ ልዩ መልክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ በበኩላቸው÷ የሮም ሚሲዮን አገልግሎቱን በግሪክ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተደራሽ ለማድረግ በአቴንስ በመገኘት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል በግሪክ የመሾሙ ሂደት እንደተጠናቀቀ እና በቅርቡም ስራ እንደሚጀመር መገለጹን የዳያስፖራ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.