Fana: At a Speed of Life!

“ስለ እናት ምድር” ፊልም ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ስለ እናት ምድር” የተሰኘ ትኩረቱን በሀገር ፍቅርና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረገ ፊልም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተመርቋል።

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ፊልሙ በሀገር ፍቅርና በሰራዊቱ ህይወት ላይ ያተኮረ ሲሆን÷ መከላከያ ሰራዊት በተለይም በሰሜኑ ጦርነት ለሀገር ሉአላዊነት መጠበቅ የከፈለውን ዋጋ የሚያሳይ ነው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

በአርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ በተዘጋጀው “ስለ እናት ምድር” ፊልም ላይ 30 ሺህ ሰዎች ተሳትፈዋልም ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.