Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ቅርሶችን ለማስመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ለጨረታ የሚቀርቡ የኢትዮጵያ ቅርሶችን ለማስመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን ብሔራዊ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

በውጭ ካሉ ቅርሶች ብዛት አኳያ ሰፊ ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ የኮሚቴው አባል አሉላ ፓንክረስት (ዶ/ር) አስገንዝበዋል፡፡

በእንግሊዝ ሀገር ብቻ በ27 ሙዚየሞች ውስጥ የኢትዮጵያ ቅርሶች እንደሚገኙ ጠቅሰው÷ ቅርሶቹን ለማስመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

በተለይም በግለሰቦች እጅ በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ለጨረታ እየቀረቡ መሆኑን አመላክተው÷ ከጨረታ በመከላከል ወደ ሀገር እንዲመለሱ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ኮሚቴው ባለፉት ዓመታት በእንግሊዝና ጣልያን በርካታ ቅርሶችን ማስመለሱንም አስታውሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.